History & Heritage
ታሪካዊ አመጣጥና አሰፋፈር
የምስራቅ ኩሻዊ (High land east Cushitic) ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ ከቀቤንኛ፣ ሲዳሙ አፎ፣ ካምባትሣ፣ ጣምባርሣና ሃዲይኛ ጋር የመመሳሰል ባህሪይ አለው፡፡ ለዚህም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች የሚሰጡት ምክንያት ታሪካዊ አመጣጣቸው ከአንድ አካባቢ መሆኑና አሁንም አጐራባቾች ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ቋንቋውን ለማሳደግ የተወሰኑ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ለአብነትም አንግሊዝኛ-አላብኛ መዝገበ-ቃላት እና “የጀርመንና-አንግሊዝኛ-ሀላብሳ መዝገበ- ቃላት”፣የሀላብሣ ቋንቋን የትምህርት መስጫ ቋንቋ ለማድረግ የሚረዳ አጋዥ መጽሐፍ (Halabisa Grammer, phonoilogy, Morphology and Syntax) በብሔረሰቦች ም/ቤት ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በተጨማሪም በቋንቋው በአንደኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በብሔረሰቡ ከአፍ መፍቻ ቋንቋው በተጨማሪ አማርኛ፣ ስልጢኛ፣ ኦሮምኛ፣ ከምብትሣና ሀዲይኛ ቋንቋዎች በሰፊው የሚነገሩ ናቸው፡፡
የሀዲያ ብሔረሰብን ቅድመ ታሪክ አስመልክቶ በብሔረሰቡ ምሁራንና በሀገር ሽማግሌዎች የተለያዩ አመለካከቶች ይንፀባረቃሉ፡፡ ከእነዚህ አመለካከቶች ውስጥ አንደኛው የሀድያ ብሔረሰብ ከእስያ ክፍለ አህጉር ተነስቶ ቀይ ባህርን አቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል የሚለዉነዉ፡በዚህ ገለፃ መሠረት ሀዲያዎች ከአረቢያ ፈልሰው ቀይ ባህርን በማቋረጥ በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ሐረር ላይ በመስፈር፣ ቀስ በቀስም ለከብቶችና ለእርሻ ተስማሚ የሆነ ለም መሬት እና ለከብቶቻቸው ውኃና የግጦሽ ሣር ፍለጋ በመንቀሳቀስ ባሌንና አርሲን አቋርጠው አሁን የሠፈሩበት አካባቢ እንደከተሙ ይታመናል፡፡ ይህን መሠል ረዥምና ውጣ ውረድ የሞላበትን ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት ጥቂት የማይባሉ የብሔረሰቡ አባላት በባሌ፣ በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች ተቆርጠው የቀሩና በአሁኑ ወቅት የኦሮምኛና የሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች ቢሆኑም በዘር ሀረጋቸው ግን ሀዲያ መሆናቸው ይነገራል፡፡
ስለ ብሔረሰቡ ታሪካዊ አመጣጥና አሰፋፈር የሚያትተው ሁለተኛው አመለካከት ደግሞ; ሀድያን ከአረቢያና ከኤስያ ጋር በማዛመድ ከትውፊት /አፈ-ታሪክ/ የዘለቀ የታሪክ መረጃ እንደሌለው በመግለፅ ሀድያ ጥንታዊና ነባር ህዝብ (indigenous) መሆኑን በአፅንኦት ከገለፀ በኋላ የመጀመሪያውን አመለካከት በከፊል በመጋራት የብሔረሰቡ ጥንታዊና ታሪካዊ መነሻ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ እንደሆነና ከሰፈረበት በሐረር በተለያዩ ሰብዓዊና ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ሳቢያ ወደ ባሌ አርሲና ሌሎች አካባቢዎች በመጓዝ አሁን የሰፈረበትን አካባቢ እንደያዘ ይገልፃል፡፡
የታሪክ ምሁር ኘሮፌሰር ላጲሶ ጌድሌቦ፣ ሁለተኛውን አመለካከት የሚጋሩ ሲሆን በ1991 ዓ.ም “የሀዲያ ሕዝብና መንግስት ታሪካዊ መነሻና ሚና በደቡብ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ በገፅ 29፣ “በደቡብ ኢትዮጵያ በምሥራቅ ከዋቤ ወንዝ፣ በምዕራብ ከጊቤ ወንዝ፣ ድረስ በሚገኘው ምድር በ15ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ የሀዲያ ሥልጣኔ /እስላማዊ መንግስት/ በአሥር ገራዶች የተከፋፈለ አሥር የአካባቢ መስተዳድሮች ወይም ክፍለ ግዛቶች የተከፋፈለ አንድ ታላቅ ጥንታዊ ሕዝብ… እንደነበር ይገልፃሉ፡፡ ስለ ሀድያ እስላማዊ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተጠቅሶ የምናገኘው በ14ኛው ክ/ዘመን በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግስት ነው፡፡ ንጉሥ አምደፅዮን /1314-1344/ ሀድያን በ1316 በወረራ ካስገበረ በኋላ ወታደር ሲመለምልበት ቆይቷል፡፡ ይሁንና ሀዲያ በንጉሥ አምደፀዮን ቢሸነፍም ለነፃነቱና ለማንነቱ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ማድረጉ ይታወቃል፡፡በመሆኑም “የሰለሞናዊው” ክርስቲያን ነገሥታት የሀድያ መሪዎችን አመጽ ለማለዘብና ለመግታት በማሰብ ፖለቲካዊተልዕኮ ያላቸው ጋብቻዎችን ከሀድያ ገራዶች ቤተሰብ ጋር በመፈፀም ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይቷል፡፡ ለአብነትም በወቅቱ ገናና ከነበረው ንጉሥ ዘርዓያዕቆብ /1434-1486/ ኋላ ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ህይወት ውስጥ ታላቅ ሚና ለመጫወት የበቃችውን የሀድያውን ገራድ መሐመድ ልጅ “ዛላን” ወይም እሌኒን /የንግስና ስሟ/ አግብቷል፡፡ በልጁና በአልጋ ወራሹ በበዕደ ማሪያም /1468-78/ እና የልጅ ልጁ በነበረው በልብነ ድንግል /15ዐ8-40/ ዘመንም ይኸው ፖለቲካዊ ጋብቻ ሲካሄድ የቆየ ቢሆንም ሀድያ ለነፃነቱና ለክብሩ ሲፈጽም የነበረውን ተጋድሎ ሊገታው እንዳልቻለ የታሪክ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡
Tourism
- ቡዳመዳ ሀይቅ ( 40 ሄክታር, ከሆሳና 108ኪሜ ሲራሮ ወረዳ, በዙሪዪው ፍልውሃ ያሉት) ፣ ጢሎ ሀይቅ (60 ሄክታር ፣ ጥልቀቱ አይታወቅም ፣ ሲራሮ ወረዳ ፣ ጨዋማ ፣ ከአዋሳ ኤርፖርት 35ኪሜ ነው ግን አስፖልት የለውም ፣ ፍልውሃ አለው) ፣ መጨፋራ ሀይቅ ( 50 ሄክታር 10 ሜትር ጥልቀት, የስደተኛ ወፎች መገኛ, ሲራሮ ወረዳ)
- ሻሎቦሎ ዋሻ ፣ ኦሊጋ ሰውሰራሽ ዋሻ
- ሀብቾ ፏፏቴ (ሀብቾ ሜዳና ሀውልት: ከያሽ ዶጆ የተባሉ ግለሰብ አራት ወንድሞቻቸው በድርቅ ከብቶቻቸው ሲያልቁባቸው ይሄንን እያየሁ አልቀመጥም ብለው ከራሳቸው ከብት ለያንዳንዳቸው 100 ከብት የለገሱበት የደግነት ሜዳ)
- ከተፈጥሮአዊ መስህቦች መካከል ፍል ውኃዎች /የሀዎራ ጠበል/ ፏፏቴዎች የገሙና፣የጐንቦራ፣የሀብቾ፣የብላቴ/ሐይቅ/፣ ቦዬ ሐይቅ ሠንሠለታማ ተራሮች/ሸንቆላ፣ቱላካላለም/ እና ተፈጥሮአዊ ገጽታዎች ለአብነት ሲጠቀሱ
- ከሰው ሠራሽ መስህቦች ታሪካዊነት ያላቸው ዋሻዎች /በንዳልቾ ኡልዳ፣ ባቴና ከራራ፣ሲቢያ፣ጋጋኖ/ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት /የጊቤ፣የመስመስ ቅ/ገብርኤል/ ባህላዊና የወግ ዕቃዎች